Miskaye Hizunan Medhanealem & Tsedenia Mariam Ethiopian Church Vancouver

Church Fundraising dinner poster-Aug26-BlueGradiantBG_WEB

“የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን” ነህ:፪፣፳

የቫንኩቨር ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለምና ፄዴንያ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ለቤተክርስቲያን ግዢ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ እራት አዘጋጅቷል!

ተጋባዥ መምህር መላከ ሠላም ቀሲስ ሰብስቤ እና ዘማሪ ሊቀ ልሳናት ቸርነት ሰናይ የሚገኙበት ታላቅ መርሐ ግብር በ Aug 26, 2023 (ነሐሴ 20, 2015) ዕለት ከ 3፡30 PM – 9፡30 PM ድረስ ይካሄዳል። በዕለቱ የተሟላ ምግብ እና መጠጥ አቅርቦት እንዲሁም ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል 

እርስዎም ትኬትዎን በመግዛት እና በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተሳታተፊ እንዲሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

Vancouver Miskaye Hizunan Medhanealem & Tsedenya St. Mary Church has organized a fundraiser dinner on August 26, 2023 – from 3:30 PM – 9:30 PM at the Bollywood Banquet Hall (8166 128 St. Surrey)

Don’t miss out on this great opportunity to support your community Church and partake in the blessings! Buy your ticket now to guarantee your spot!

Who we are

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለምና ጼዴንያ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በአጭሩ፡፡

ከ፲፱፻፺፯ ዓ.ም ቀደም ባሉት አመታት በግለሰብ ቤት በጥቂት ሰዎች ዝክርና መታሰቢያዎችን በማድረግ የተጀመረው መርሐ ግብር ከግዜ ወደ ግዜ እየሰፋ በመሄዱ በመጀመሪያ 63st/Fraser በሚገኘው የሰርቢያን ኦረቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመሰባሰብ በካሴት እየተቀደሰ አገልግሎቱ ተጀመረ፡፡ ሲመሰረት ጀምሮ አቡነ ዜና ማርቆስና አባ ወልዴ የዛሬው አቡነ ሉቃስ ከሲያትል ፣ 
ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ከቶሮንቶ በመመላለስ መንፈሳዊ ትምህርት በመስጠት፣ ምእመኑን በመምከርና በማደራጀት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

የቤተክርሰቲያናችን መስራቾች ቀደም ብለው ከሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ጋር በነበራቸዉ ቅርበት የተነሳ ቤተክረሰቲያኒቱን ህጋዊ ለማድረግ በጠየቁት እርዳታ መሰረት በ1995 (እኤአ) የመጀመሪያዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን በቫንኮቨር እንደ ቅርንጫፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በካናዳ  በሚል ህጋዊ መጠሪያ ባለዉ የቶሮንቶ ቤተክረሰቲያን ስር  ተመሰረተች።

CONTACT

628 Royal AvenueNew Westminster, British Columbia

Call (604) 256-0217

መልክት ይላኩልን ወይም መተው ይጎብኙን

Please drop by or leave us a message.