የዘወትር ሰንበት ቤተክርስቲያኑ ከሌሊቱ 4 am ለምእመናን ክፍት ቢሆንም ቅዳሴ ከጧቱ 6am ጀምሮ እስከ 9:30am ይጠናቀቃል፡፡ ዘወትር ከቅዳሴ በኋላ መዝሙር በህጻናትና ወጣቶች ከቀረበ በኋላ የእለቱ ትምህርት ይቀርባል፡፡
ዘወትር እሁድ ከቅዳሴ በኋላ ከ 10 am – 11am በእንግሊዘኛ የህጻናትና ወጣቶች የተከታታይ ትምህርት ይሰጣል፡፡
በአጥብያችን ሁለት የንግስ በአላት አሉን፡፡ አንደኛው በመስከረም አሥር የሚከበረው የጼዴንያ ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ በአል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መጋቢት 27 የሚከበረው የመድሐኔዓለም አመታዊ በአል ናቸው፡፡ ከሀገሩ አኗኗር የተነሳ ብዛት ያላቸው ምእመናን እንዲገኙ በማሰብ በአላቶቹ የሚከበሩት እንደ አመቺነቱ ቅዳሜ ወይም እሁድ ይሆናል፡፡ በአላቶቹ ዋዜማውን በልዩ ልዩ የስብከተ ወንጌል መርሀግብር ስናከብር ሌሊት 1am ጀምሮ በማህሌት ይከበራል፡፡
የሰሙነ ሕማማት ዓመታዊ አገልግሎት እንደተጠበቀ ሁኖ ዘወትር የስቅለት በአል በሚከበርበት ዓርብ ከጧቱ 6am – 6pm አገልግሎት ይሰጣል፡፡
የዳመራ በዓል ዓመታዊ አገልግሎት መስከረም ፲፮ ቀን በዋለ በሚቀርበው እሁድ ከቀኑ ፱ ሰዓት እስከ ምሽቱ ፲፪ ሰዓት Trout Lake በሚባለው ስፍራ ከሌሎች አጥብያ ጋር በጋራ ይከበራል
ከዚህ በተጨማሪ የስብከተ ወንጌልና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እንደየአመቺነቱ ይካሄዳሉ፡፡